EthiopiaNews

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2027 በ7 ነጥብ 8 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ትንበያውን አስቀመጠ።

ድርጅቱ ይሄን ያለው የአለም ኢኮኖሚ በተመለከተ ዛሬ ባወጣው አመታዊ ሪፖርቱ ላይ ነው።

የገንዘብ ድርጅቱ በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ9 ነጥብ 2 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ትንበያውን ይፋ አድርጓል።

ርዕሰ ብሔር ታዬ አፅቀ ስላሴ ዘንድሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።

የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ መዲና ባንኮክ ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ነው።

የገንዘብ ድርጅቱ የአለም ኢኮኖሚ በአማካይ በ3 ነጥብ1 በመቶ እድገት ሊያስመዘግብ ይችላል ብሏል።

መረጃው ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘ ነው።