EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከመስከረም 15 ቀን ጀምሮ በከተማዋ በሞተር ብስክሌቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ።

ፖሊስ እገዳውን የጣለው፣ በሞተር ብስክሌቶች አማካኝነት ወንጀሎች እየተፈጸሙና ደንቦች እየተጣሱ መኾኑን በመጥቀስ እንደነበር ይታወሳል።

ፖሊስ የሞተር ብስክሌቶች መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃድ ያደሱ አሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ መፈቀዱን አስታውቋል።

ፖሊስ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።