EthiopiaNews

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 309 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት 2 ነጥብ 224 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የነበረ መሆኑን እና አፈጻጸሙ 103 ነጥብ 82 በመቶ መድረሱን ገልጿል።

ይህም ከዕቅዱ በ85 ነጥብ 01 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 836 ነጥብ 658 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸርም፣ የዘንድሮው አፈጻጸም በ176 በመቶ ማደጉን ገልጿል።

በሁለቱ ወራት ከተገኘው ገቢ ውስጥ ከማዕድን ዘርፍ 1 ነጥብ 346 ቢሊዮን ዶላር እና ከግብርና ምርቶች ዘርፍ 837 ነጥብ 989 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

በሁለቱ ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ ንግድ 50.07 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም የዕቅዱን 124.30 በመቶ ያሳካ ነው።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።