EthiopiaNews

ቡልጋሪያን በሚያዋስነው የጥቁር ባህር ክልል አንዲት መርከብ በድሮን ተመታ ሰምጣለች።

የቡልጋሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሜን ራዴቭ እንዳሉት ንብረትነቷ የዩክሬን ብትሆንም በማልታ የተመዘገበችው ቼልሲ የተባለችው መርከብ በሦስት ድሮኖች ተመታለች።

ከአደጋው በኋላ በመርከቧ ያሉ 15 ሰራተኞች በነፍስ አድን ሥራ መርከቧ ከመስመጧ በፊት ሊወጡ ችለዋል።

አንዲት ሌላ መርከብም ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶባት የነበረ ቢሆንም ጉዳት ደርሶባት ከመስመጥ ተርፋለች።

ጉዳዩን በቀላሉ አናየውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉዳይ ላይ ከኔቶ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጋር እንመክራለን ብለዋል።

ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ባይኖርም አደጋው የደረሰበት ጥቁር ባህር የሩሲያና ዩክሬን የውጊያ ግንባር እየሆነ መጥቷል።