የገንዘብ ሚኒስቴር ለተያዘው የ2019 በጀት ዓመት ሁለተኛው ሩብ ዓመት 133 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የግምጃ ቤት ሠነድ ጨረታ አወጣ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው የግምጃ ቤት ሠነድ ጨረታ መርሃ ግብርን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
የግምጃ ቤት ሠነዶቹ የ28 ቀናት፣ የ91 ቀናት፣ የ182 ቀናት እና የ364 ቀናት እድሜ ያላቸው መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ስቴሩ ከጥቅምት 4 እስከ ታኅሳስ 14 2019 አ.ም ድረስ ስድስት የግምጃ ቤት ሠነድ ጨረታዎችን እንደሚያወጣ ገልጿል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
