የአለም የጤና ድርጅት 71 ቶን መድሃኒት ፣ የመድሃኒት ቁሳቁሶች እና ሌሎች ግብአቶችን በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ማድረሱን አስታወቀ።
የጤና ድርጅቱ ይሄን ያለው በኤክስ የትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።
የጤና ድርጅቱ የሰብአዊ ድጋፉ በግጭት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ነው ብሏል።
የመንግስታቱ ድርጅት የህፃናት መርጃ ( ዩኒሴፍ) ልዩ ልዩ የሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ መኪኖች ትናንት ወደ መቐለ መግባታቸውን መግለጹ ይታወሳል።
