EthiopiaNews

ባለስልጣን መ/ቤቱ በቸልተኝነት በወንዞችና በወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁና ያለፈቃድ ፍሳሽ ቆሻሻን ከፍሳሽ ማስወገጃ ጋር አገናኝተው የለቀቁ 3 ተቋማትን የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ ያልተጣራ ፍሳሽ ወደ ወንዝ የለቀቀው ሴንቸሪ ሪል እስቴት እና የተቋሙ ፍሳሽ ቆሻሻ ያለፈቃድ ከፍሳሽ ማስወገጃ ጋር አገናኝቶ የለቀቀው ኦላ ማዲያ የመኪና እጥበት እያንዳንዳቸው 400,000 ብር እንዲሁም በለስ ህንፃ ያልተጣራ ፍሳሽ ከውሃ መውረጃ ጋር በማገናኘት 300,000 ብር ተቀጥተዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ በቸልተኝነት የደንብ መተላለፍ የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።