የብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን በትግራይ ከ18 ሺ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ተሐድሶ ማእከላት ለመግባት መመዝገባቸውን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብ/ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው ይሄን ያሉት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል (ዲዲአር ) መርሃ ግብር አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ነው።
ምክትል ኮሚሽነሩ በመቐለ ከ15 ሺ በላይ እንዲሁም በሽረ ከ3ሺ የሚበልጡ የቀድሞ ታጣቂዎች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በትግራይ እደጋ ሐሙስ እና ማይጨው ከተሞች ያሉ ተጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማእከላት ለመግባት ምዝገባ እያካሄዱ ነው ተብሏል።
ምክትል ኮሚሽነሩ በትግራይ ክልል ከጥቅምት 12 ቀን 2019 አ.ም ጀምሮ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማእከላት መግባት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።
