የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1.432 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማግኘት መቻሉን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ይሄን ያለው የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው።
ኮሚሽኑ በሩብ ዓመቱ 900 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለማግኘት ታቅዶ 1.432 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልፆ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ49 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል።
በአዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶች በኩል 123 ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ 179 አዳዲስ ፈቃዶች የተሰጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 122ቱ ከልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውጭ እንዲሁም 57ቱ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የተመዘገቡ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ45.5 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።
በሩብ ዓመቱ 81 ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ የተሸጋገሩ ሲሆን፣ 66 ፕሮጀክቶች ደግሞ ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል፤ ይህም አፈጻጸሙ ከ100 በመቶ በላይ ሆኖ መመዝገቡን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በሩብ ዓመት ውስጥ ከወጪ ንግድ 238 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት የተቻለ ሲሆን፣ ይህም የእቅዱን ከ100% በላይ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘ ነው።
