የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፣ የሩሲያ እና የዩክሬንን የዓመታት ግጭት ለማቆም በቀረቡት የሰላም ሃሳቦች ላይ ለመምከር ሴንት ፒተርስበርግ ገብተዋል።
ልዩ መልዕክተኛው ዊትኮፍ ወደ ሩሲያ ያቀኑት በኦስሎ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ያደረጉትን እና ዋይት ሀውስ አዎንታዊ ሲል የጠራውን የሰላም ውይይት ባጠናቀቁ ማግስት ነው።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቀደም ሲል ዋሽንግተን ወታደራዊ መረጃዎችን እየከለከለችኝ ነው በማለት ያቀረቡትን ክስ በማንሳት፥ በአሁኑ ወቅት ግን የአሜሪካ የደህንነት መረጃ መጋራት ሥርዓት በጥሩ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በበኩላቸው ክሬምሊን የአሜሪካውን መልዕክተኛ ሃሳብ ለመስማት ዝግጁ መሆኑን ቢገልጹም፥ ሀገራቸው ግን ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ስምምነት እንደማታደርግ በይፋ አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ የምታደርገውን ጥቃት በመኮነን ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም በድጋሚ የጠየቁ ሲሆን፥ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው የሰላም ጥረትም ቀጣይ ምላሽ ከሩሲያ ይጠበቃል ተብሏል።
