የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን የአሜሪካን ዶላር በ159 ብር ከ70 ሳንቲም መሸጡን አስታውቋል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የተመዘገበው ውጤት ባንኩ ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ ከተመዘገበው በ40 ሳንቲም ቅናሽ ያሳየ ነው፡፡
በዚሁ 30ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ160 ብር ከ10 ሳንቲም መሸጡም ይታወሳል፡፡
በዛሬው የ140 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ ከተሳተፉት 30 ባንኮች ውስጥ 28ቱ አሸናፊ መሆናቸውን የገለጸው ባንኩ ከ150 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፍላጎት የታየበት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ባንኩ በቀጣይ በየ ሁለት ሳምንቱ በሚያካሂዳቸው 4 የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች በእያንዳንዱ ጨረታ 140 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለባንኮች እንደሚያቀርብም ይጠበቃል።
