ኢትዮጵያ በቀጣይ 10 ዓመታት አሁን ላይ ያለውን የ44 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ወደ 100 ለማሳደግ ማቀዷ ተነገረ፡፡
በእነዚህ አስር ዓመታት ውስጥም 32 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን ዕቅዱን ለማሳካትም 18 ቢሊዮን ዶላር በጀት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የውኃ ኢነርጂ ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው የውኃ እና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ይፋ የተደረገው ይህ ስትራቴጂ በተለይ በስፋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኘ ያልሆነውን የገጠሩን ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡
