የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ይፋዊውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድረ-ገጽን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
ፅ/ቤቱ ዓለም ከስሟ ባሻገር እንቁ ታሪኳን በሙሉ ጠንቅቆ ያላወቀላት ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ታሪኳን በራሷ ድምፅና በራሷ ብዕር ለዓለም ታስተዋውቃለች ብሏል።
ይህ ድረ-ገጽ ከታሪካችን እስከ ዛሬ እርምጃችን፣ ከሥልጣኔያችን እስከ የወደፊት ርዕያችን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሀብትና ተስፋ ለዓለም የምናቀርብበት መድረክ ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ገልጿል።
በዚህ 🔗 ማስፈንጠርያ በመጠቀም ይፋዊውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድረ-ገጽ ገፅ መመልከት ይችላሉ። : https://ethiopia.gov.et/
መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።
