InternationalNews

የአሜሪካ አየር መንገዶች መንገደኞች ወደ አሜሪካ ሲመጡ ወደ ዲሞክራቲክ ኮንጎ አለመሄዳቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዲያቀርቡ የሚያስገድደው መመሪያ እንዲነሳ ጠየቁ ።

የአየር መንገድ ማኅበራቱ ለአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ መስሪያ ቤት  በላኩት ደብዳቤ፥ በመጪው ህዳር ይተገበራል የተባለው ይህ አዲስ መመሪያ እጅግ አድካሚ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ተጨማሪ ወጪ የሚያስከትል መሆኑን ገልጸዋል።

የአየር ትራንስፖርት ድርጅቶች ይህንን ሕግ አየር መንገዶች ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የቴክኖሎጂ አሠራራቸውን ቀይረው እንዲተገብሩት በጤና ጥበቃ መስሪያ ቤቱ መጠየቁ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ፥ በተለይ የአውሮፕላን ሰራተኞች እና የጦር ኃይል አባላት ከዚህ ደንብ ነፃ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

አየር መንገዶቹ ባለፈው ዓመት ወደ አሜሪካ ከገቡት 130 ሚሊዮን መንገደኞች መካከል ከኮንጎ ጋር ንክኪ የነበራቸው ከ25 ሺሕ ያነሱ መሆናቸውን በመጥቀስ፥ አዲሱ አሰራር ከችግሩ መጠን ጋር የማይመጣጠን መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ባለፈው ግንቦት ወር በኮንጎ የተቀሰቀሰውና እስካሁን በአፍሪካ ወደ 4 ሺህ 700 ሰዎችን የገደለው ኢቦላ ፥ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት  ሕክምናም ሆነ ክትባት እንደሌለው ይገለጻል።