EthiopiaNews

የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መክፈል እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡

የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ አረጋይ የደመወዝ ክፍያውን ለማስፈጸም የፋይናንስ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በሥራ ቦታቸው ተገኝተው ሥራ መጀመራቸውን ሪፖርት ላደረጉና በሕጋዊ ሁኔታ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥረው ለሚሠሩ ሠራተኞች ደመወዝ እንደሚከፈልም ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡

የደመወዝ ክፍያው መጀመር በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ሥራ መልሶ ለማስጀመርና የሠራተኞችን የሥራ ተነሳሽነት ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ መሆኑን ነው አክለው የገለጹት፡፡