መንግስት ላለፉት 2 ዓመታት ከ3 ወር ከብሄራዊ ባንክ ምንም ብድር አለመውሰዱ የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት አስተዋጽኦ ማድረጉን ብሄራዊ ባንክ ገለጸ፡፡
ባንኩ 8ኛውን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባና ውሳኔዎችን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሲሰጥ ነው ይህን የገለጸው፡፡
የበጀት ፖሊሲ ስርዓቱ ጥንቃቄ የተሞላበትና ከብሄራዊ ባንክ ጥብቅ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ከአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ጋር የተናበበ መሆኑን ኮሚቴው መገንዘቡንም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
የኮሚቴውን ስብሰባ ግምገማዎችና ውሳኔዎችን ወደ በኋላ ላይ በዝርዝር የምንመለስባቸው ይሆናል፡፡
