EthiopiaNews

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን “የትግራይ ሚዲያ ኮርፖሬሽን” በሚል አዲስ ስያሜ ሕጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የትግራይ ቴሌቪዥን ዛሬ ወደ መደበኛ ሥርጭት መመለሱን አስታወቀ።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቀድሞው የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን የሚቃረኑ፣ ይዘቶችን ሲያሠራጭ በመገኘቱ ፈቃዱ መታገዱን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ተቋሙ ለክልሉ ሰላም እና መረጋጋት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እና የሕዝብ ድምፅ እንዲሆን በማሰብ ባደረገው ጥረት፣ ተቋሙ በአዲስ መዋቅር እና አቅጣጫ እንዲዋቀር ተደርጓል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለተቋሙ “ትግራይ ሚዲያ ኮርፖሬሽን” በሚል አዲስ ስያሜ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን ተቋሙ በዛሬው ዕለት ወደ ሥርጭት ተመልሷል ተብሏል።