InternationalNews

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ፤ ሪፐብሊካን ፓርቲ የኮንግረሱን የድምጽ የበላይነት ያጣው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት ውሳኔ ምክንያት መሆኑን በይፋ በመግለጽ፣ እራሳቸውን ከዚህ የውጭ ፖሊሲ መስመር ማራቃቸውን አስታወቁ።

ጄዲ ቫንስ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሪፐብሊካን ፓርቲ በምርጫው የተሸነፈበት ዋነኛው ምክንያት የኢራን ጦርነት መሆኑን በመጥቀስ፣ ከኢራን ጋር ለመዋጋት ተብሎ ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት የሴኔት ምክር ቤት አብላጫ ወንበርን ለዲሞክራቶች አሳልፎ መስጠት ትልቅ ኪሳራ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የቫንስን የትችት አስተያየት እንደሚረዱት በመግለጽ፤ ዋሽንግተን እና እስራኤል በጋራ የሰነዘሩት ወታደራዊ ጥቃት ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታገኝ ያገደ በመሆኑ የተወሰደው እርምጃ ትክክለኛ እንደነበር ለጋዜጠኞች በሰጡት ምላሽ ተከላክለዋል።

የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን የጄዲ ቫንስ መግለጫ የ2028ቱን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ለመጀመር እና እራሳቸውን ከትራምፕ የውጭ ፖሊሲ መስመር ለመለየት ያደረጉት ጥረት እንደሆነ እየገለጹ ይገኛሉ።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፓርቲያቸው በድጋሚ እንዲያሸንፍ ይረዳሉ ያሏቸውን አራት ዋና ዋና የፖለቲካ ግቦች ያስቀመጡ ሲሆን፤ እነሱም የኢራንን ጦርነት ማቆም፣ በኑሮ ውድነት እና በዋጋ ግሽበት ላይ ማተኮር፣ «አሜሪካን ማስቀደም» እንዲሁም ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት መለወጥ የሚሉ መሆናቸው አመልክተዋል።