የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመዲናዋ ላሉ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ እድሳት ታኅሣሥ 30 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
ቢሮው ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
ቢሮው የመዲናዋ ነጋዴዎች ከታኅሣሥ 30 ቀን 2019 ዓ.ም. በፊት ባሉበት ሆነው በኦንላይን አገልግሎቱ የንግድ ፈቃዳቸውን በማደስ፣ በመጨረሻ ሰዓት ሊያጋጥም ከሚችል የሲስተም መጨናነቅና ከአላስፈላጊ ቅጣት እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።
የንግድ ፈቃዳቸውን ለማደስ የሚፈልጉ ነጋዴዎች በዚሁ ሊንክ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።http://www.etrade.gov.et
በከተማዋ የሚገኙ ነጋዴዎች ሁሉ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት የ2019 ዓ.ም. የንግድ ፈቃዳችሁን በኦንላይን እንዲያድሱ ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘ ነው።
