InternationalNews

በኢራን ይደገፋሉ የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በብሪታንያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ለመፈጸም ማሴራቸውን የአሜሪካ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፍትሕ ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው ክስ፤ ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው መስከረም ወር በብሪታንያው ፌርፎርድ አየር ኃይል ሰፈር አቅራቢያ በተከሰተው አጠራጣሪ የመኪናዎች እንቅስቃሴ ሴራ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።

ግለሰቦቹ ባለፈው ዓመት በአውሮፓ በተለይም በብሪታንያ ለተፈጸሙ 18 የእሳት ቃጠሎ፣ የቦምብ እና የስለት ጥቃቶች ኃላፊነት የወሰደ ቡድንን በማስተባበር ተከሰዋል።

አንደኛው ተጠርጣሪ በኒውዮርክ እስር ቤት ሆኖ ለተባባሪዎቹ ሚስጥራዊ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ተመሳሳይ ተግባር ከኢራን ሆነው ሲፈጽሙ ቆይተዋል ነው የተባለው።

በለንደን የሚገኘው የኢራን ኤምባሲ በበኩሉ ክሱን መሠረተ ቢስ ሲል ያጣጣለው ሲሆን፤ አሜሪካ ግን የጥቃት ስጋት አለብኝ ካለች በኋላ ሁሉንም ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቿን ከሰፈሩ አስወጥታለች።