InternationalNews

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር  ወታደሮቿ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማዘዟን ተከትሎ፤ ቴህራን ጥቃት ከተፈጸመባት ጦርነቱን ከቀጠናው ባሻገር እንደምታሰፋው በይፋ አስጠንቅቃለች።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሚመራው የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ፤ ጦሩ በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት ዝግጅቱን እንዲያፋጥን ትዕዛዝ ማስተላለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህ መመሪያ ይፋ የሆነው አዲስ መንግሥት እንዲመሠርቱ የተመረጡት ጋዲ አይዘንኮት፤ ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር  ቀጥተኛ ስጋት በሌለበት ሁኔታ ጦሩን እንዳያሰማሩ ካሳሰቡ በኋላ ነው።

የኢራን የደህንነት ኃላፊ ሞህሴን ረዛኢ በበኩላቸው፤ አሜሪካ አዲስ ጦርነት ከጀመረች ከምዕራብ እስያ እስከ አውሮፓ ያሉ ወታደራዊ ሰፈሮች ኢላማ ይሆናሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቴህራን ኒውክለር ማምረቻ የበለጸገ ዩራኒየሟን ወደ ሦስተኛ ሀገር እንድታዛውር የቀረበላትን የአሜሪካ ሀሳብ ውድቅ ማድረጓን ተከትሎ፤ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።