EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ፋይናንስ አስተዳደር አፈፃፀም ምዘና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ሊካሄድ መሆኑን የከተማዋ ፋይናንስ ቢሮ ገለፀ፡፡

ቢሮው ዓለም ባንክ በየአራት ዓመቱ የሚያካሂደውን ይህ ምዘና በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የቅድመ ዝግጅት ወርክሾፕ ያካሄደ ሲሆን ባንኩ የከተማ አስተዳደሩን የቅርብ ሶስት ዓመታት የፋይናንስ እንቅስቃሴ በመገምገም ውጤት እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ግምገማው 7 ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች፣ 31 የአፈጻፀም አመላካቾችና 94 ዝርዝር መስፈርቶች ያሉት መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ተሳታፊ ተቋማት የራሳቸውን ድርሻ ወስደው መዘጋጀት እንዳለባቸውና ባለሙያዎችም ሰነዶችን በማደራጀት በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸውም ቢሮው አሳስቧል።