EthiopiaNews

በመቐለ ከተማ 80 በመቶ የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከፖሊስ አባላት ጋር በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሙሉ አብረሃታ ውይይቱ ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀልን የመከላከል አቅምን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር ከንቲባ ሺሻይ አማረ የፖሊስ ተቋም ከየትኛውም ተቋም በላይ የማህበረሰቡን ችግር በቅርበት የሚያውቅና ለሕዝብ ከፍተኛ ውግንና ያለው መሆኑን አንስተዋል።