ቡናና ሻይ ባለስልጣን ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 4 ወራት 167.8 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 1.16 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታወቀ።
ይህ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ24.6 ሺህ ቶን፣ በገቢ ደግሞ የ157.2 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያሳየ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነትን ለማስፋት እና የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ያላሰለሰ ጥረት የሚያመላክት መሆኑንም ነው ባለስልጣኑ የጠቀሰው፡፡
