EthiopiaNews

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በግብፅ ጫና ምክንያት በትንሹ 22 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች መሰረዛቸውን ተናገሩ።

በግብፅ ጫና ሳቢያ በቆሙት ፕሮጀክቶች ምክንያት ኢትዮጵያ ገንዘብ መታጣቷን የተናገሩት ሚኒስትሩ በወቅቱ ፕሮጀክቶቹ ቢሰሩ ኖሮ ያጋጠመን ድርቅ እና ያጣናቸውም ህይወት አናጣቸውም ነበር ብለዋል።

ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ይህንን የገለጹት ሚኒስትሩ የተቋቋመው ብሔራዊ የጉዳት እና የካሳ ኮሚቴ አለም አቀፍ ተሞክሮ ላይ መሰረት አድርጎ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በኮሚቴው እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ግብፅ የምትከፍለው ነገር እንደሚኖር ጠቅሰው በገንዘብ ይሁን በሌላ በሂደት የምናየው ነው ብለዋል።