ኢትዮጵያ፣ ቻይና እና ቱርክ ሃገራት የካርበን ልቀትን በቀነሱበት መጠን ልክ ክፍያ የሚያገኙበት አሰራር እንዲቀላጠፍ የሚያግዝ አዲስ ኢንሼቲቭ ይፋ አደረጉ።
ይህ የ3ቱ ሃገራት ኢንሼቲቭ ይፋ የተደረገው በመካሄድ ላይ ባለው 31ኛው የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ነው።
ሃገራት የካርበን ልቀትን በቀነሱበት መጠን ልክ ክፍያ የሚያገኙበት አሰራር እንዲቀላጠፍ የሚያግዝው ኢንሼቲቭ የተመድ ከፍተኛ እና የአለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በገኙበት በአንታሊያ የቻይና ፓቪሊዮን ላይ ይፋ ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቻይና የስነ ምህዳር እና አካባቢ ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር ሊ ጋኦ መንግስታት አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የሚመለከታቸው ተቋማት ይፋ የተደረገውን ኢንሼቲቭ እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ዥንዋ ዘግቧል።
