የአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል በተከሰተው ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ 7 ሺህ 200 ሰዎች አስፈላጊ እርዳታ መሰጠቱን አስታወቀ።
ኮሚቴው ባወጣው አጭር መግለጫ ድጋፉ የተደረገው የአለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የመስክ ቡድኖች በክልሉ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑንም ጠቅሷል፡፡
በክልሉ የተለያዩ የነፍስ አድን ስራ እየሰራ መሆኑን የገለጸው ኮሚቴው በቅርቡም በቅርቡ በትግራይ ክልል ለ33 የጤና ተቋማት የመድኃኒት እና የመድሃኒት ግብአት ድጋፍ ማድረጉም ጠቅሷል።
