InternationalNews

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል ዛሬ በባህሬን የሚገኝ የአሜሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ራዳር ጣቢያን መምታቱን አስታወቀ።

ኃይሉ በኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ባወጣው መግለጫ ይህ እርምጃ በደቡባዊ ኢራን በሚገኝ የቴሌኮሙኒኬሽን ማማ ላይ ለተፈጸመው የአየር ጥቃት የተሰጠ የአጸፋ ምላሽ መሆኑን ገልጿል።

ይህ የኢራን የጥቃት መግለጫ የወጣው ባለፈው የካቲት ወር በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተጀመረው ጦርነት በአንጻራዊ ሁኔታ ጋብ ባለበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል።

ካለፈው መስከረም ወር መጀመሪያ ወዲህ ቴህራን በባህረ ሰላጤው አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ንብረቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ስትገልጽ ይህ የመጀመሪያዋ ነው።

የአሜሪካም ሆነ የባህሬን መንግሥታት ኢራን ስላወጣችው የጥቃት መግለጫ እስካሁን የሰጡት ምላሽ የለም።