በመዲናዋ የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓት በይፋ ሥራ ላይ መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ተፈራ ሞላ ቴክኖሎጂው በከተማዋ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ በድሉ ሌሊሳ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር በሰው ንክኪና በተቆጣጣሪዎች እጅ ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆኑ ለተለያዩ እንከኖችና አድልዎ ይዳርግ እንደነበር አንስተዋል፡፡
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ የተሽከርካሪ ምደባ፣ የተቆጣጣሪ ምደባ፣ የሠራተኞች ክትትል፣ የተገልጋይ ጥቆማ፣ የሴክተር ሪፖርት እንዲሁም የአውቶቢስ ዕለታዊ ክስተት ሪፖርቶችን በአንድነት አካትቶ የያዘ መሆኑም ተገልጿል።
