የጤና ሚኒስቴር የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከአሜሪካ መንግሥት የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የልኡካን ቡድን ጋር በፕሮጀክቱ ቁልፍ ስኬቶችና ቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።
የአሜሪካ መንግሥት የአቅርቦት ሰንሰለት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የጤና ግብዓቶች አቅርቦት አስተማማኝነት እያሳደገ እንደሚገኝ ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
ዶ/ር መቅደስ ዳባ በውይይቱ የፕሮጀክቱን ተግባራት ማስፋፋት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በኤችአይቪ/ኤድስ፣ በወባ፣ በሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) እንዲሁም በእናቶች፣ ጨቅላ ሕፃናትና ሕፃናት ጤና መርሃ ግብሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ የሀገር ውስጥ የሎጂስቲክስ አቅራቢዎችን ጨምሮ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ ልዑካን ቡድኑን የመሩት ጆናታን ሮስ ገልጸዋል።
መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
