የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሥነ-ምግባር ጉድለት ያሳዩ 60 ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
ቢሮው ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
ቢሮው በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እርምጃ ከወሰደባቸው 60 ሰራተኞች ውስጥ ከባድ ጥፋት የፈጸመ አንድ ሠራተኛ ከሥራ ተሰናብቷል ተብሏል።
እርምጃው ከዋናው መሥሪያ ቤት እስከ ወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ ያሉ የሥራ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ተሾመ ኢደቲ ገልጸዋል።
ጤናማ የሥራ ባህል ለመገንባትና የሙስና ተጋላጭነትን ለመቀነስ ለሠራተኞችና ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች መሰጠቱን ነው ቢሮው ያስታወቀው።
በቢሮው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በቴክኖሎጂ ልማት የተጀመሩ ሁሉአቀፍ የሪፎርም ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
