EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ ሽረ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አየር መንገዱ ይሄን ያለው ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

የአየር መንገዱ ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የአየር መንገዱ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከል 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ባለፈው መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሽረ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡ ይታወሳል።