EthiopiaNews

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ በሚያስፈልገው ደረጃ፣ በተደራሽ መንገዶች እና ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ አቀረቡ።

ከኮፕ 31 ጉባኤ ጎን ለጎን ከዉጥን ወደ ተግባር በሚል ሀሳብ በተካሂደው መድረክ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ሀገራዊ ዉጥኖችን ወደ ተግባር ለመቀየር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሀብቶች በቂ በማይሆኑበት ጊዜ ትግበራ እንደሚዘገይ፣ ተጋላጭነት እንደሚባባስ እና በጋራ ጥረት ላይ የሚኖረው እምነት እንደሚዳከም የገለጹት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡