EthiopiaNews

ዓባይ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለስድስት ድርጅቶቹ የ430 ሚሊዮን ብር የፋይናንስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ዓባይ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ተቋሙ ሁሌም ‘አዲስ ፕሮጀክት’ በማቋቋም ላይ ብቻ እንደማያተኩር ገልፆ አስቀድመው በተፈጠሩ እምቅ አቅሞች ላይ መልሶ ካፒታል በማፍሰስ ነባር ሀይል ያደረጃል ብሏል።

ተቋሙ የተበታተነውን የአማራ ክልላዊ መንግስት ኢንቨስትመንት አቅም ወደ ተደራጀ ሀይል እንደሚለውጥ ገልጿል።

ተቋሙ ለ6 ድርጅቶቹ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረጉን ነው ያስታወቀው።

በዚህም
1 •⁠ ⁠ገንዳ ውኃ የጥጥ መዳመጫ ኃ/የተ/የግ/ማህ- 160 ሚሊዮን ብር

2 .ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ አ/ማ -100 ሚሊዮን ብር

  1. የጎፍ የእንጨት ውጤቶች ማምረቻና ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ -40 ሚሊዮን ብር

4 . ደብረ ብርሃን ፕሪ-ኢንጂነርድ ሶሉሽንስ አ/ማ -40 ሚሊዮን ብር

  1. ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህ (የአበባ እርሻ ልማት) – 60 ሚሊዮን ብር

  2. ተላጀ ጋርመንት ኃ/የተ/የግ/ማህ -30 ሚሊዮን ብር