EthiopiaNews

የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ባለፉት 2 ሳምንታት 35 ነጥብ 6 ሜትሪክ ቶን የመድሃኒት እና የንፅህና ግብአቶችን ለትግራይ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ድጋፉ በትግራይ ክልል ሽረ ፣ሽራሮ እና አስገደ ወረዳ ለሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች እና በርካታ የጤና ተቋማት መዳረሱ ነው የተገለፀው።

የድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ከላይ በተጠቀሱት የጤና ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው ላሉ ሕሙማን እስከ 6 ወር የሚዘልቅ የምግብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል።

ቡድኑ ለትግራይ የጤና ተቋማት የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።