EthiopiaNews

በኢትዮጵያ መድኃኒቶችና ክትባቶች ከክልል መጋዘኖች ተነስተው በገጠርና በከተማ ወደሚገኙ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች እንዲሁም እስከ ታካሚው እጅ ሳይበላሹና በወቅቱ የሚደርሱበትን ምጣኔ ከ33 በመቶ ወደ 77 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ተነግሯል፡፡

ይህ የተነገረው ትናንት አለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ጉባኤ በተጀመረበት መሰናዶ ላይ ሲሆን ከተደራሽነት የራቁትን 23 በመቶ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ የግል ባለሃብቶች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ በሩን ከመክፈት ባለፈ በሃገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉ የድሮን ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ 8 በመቶ የነበረውን በሃገር ውስጥ የሚመረት መድሃኒት የመግዛት ድርሻ አሁን ላይ ወደ 44 በመቶ ማደጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የጤና ስርአት ከ130 ሚሊየን በላይ ህዝብ እያገለገለ መሆኑን አንስተው ከእነሱ መካከል 70 ሚሊየኑ በማህበረሰብ ላይ የተመሰረተ የጤና መድን  የተሸፈኑ ናቸው ብለዋል።