ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት መንግስት 454 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት አሁን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አጠቃላይ ገቢ 454 ቢሊየን ብር መገኘቱን ጠቅሰው የመንግስት ወጪ ደግሞ 458 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልፀዋል።
ከሞላ ጎደል ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ ተጨማሪ ብድር ሳንጠይቅ በገቢያችን ልክ ወጪ ለማውጣት የሞከርንበት ጊዜ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአጠቃላይ ወጪ ውስጥ 88 ቢሊየን ብር ለብድር ወይም ለእዳ ክፍያ የዋለ ነው ብለዋል፡፡
