EthiopiaNews

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ባለባቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሠራተኛ ማግኘት ትልቅ ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

በሀገሪቱ ያለው ስራ እጥረት እንዲቀረፍ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሥራ የለም” ቢባልም ሥራ ኖሮ ሠራተኛ የሚታጣባቸው ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በተለይም በሹፌርነት፣ በቀለም ቅብ፣ በጽዳት፣ በወለል ንጣፍ እና በሌሎች ትናንሽ በሚባሉ የሥራ መስኮች በቀላሉ ሰው አግኝቶ ማሰራት አስቸጋሪ በመሆኑ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ሰው እየተወሰደ ፕሮጀክቶችን ለማሰራት መገደዱን ጠቅሰዋል።

በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ ሠራተኛ አጥተን እስረኞች አውጥተን በቀን 500፣ 600፣ 700 ብር እየከፈልን በአንድ ቀን ነው የምናሰራው እስረኞች ራሳቸው ‘ደከመን አንሰራም’ ወደሚል ደረጃ ደርሰዋል ሲልም ጠቅሰዋል፡፡

በቀን እስከ ስድስት መቶ ብር የሚከፈል ሥራ ባለበት ሁኔታ በወር ሃያ እና ሃያ አምስት ቀን በመስራት የሚገኘውን ገቢ ንቀው “ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ የለም” በሚል የሚሰደዱ ዜጎች ምን ሊሰሩ እንደሚሄዱ ሊጤን ይገባልም ነው ያሉት።