EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮይሻ ግድብ በዚህ አመት ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ትናንት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ወጪን ለመቀነስ በተለያዩ ደረጃዎች ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመው፣ የኢንዱስትሪ ዋና ግብዓት ከሆነው ኢነርጂ አንጻር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ኮይሻ በአፍሪካ ሶስተኛው ግድብ መሆኑን እና ከ2 ሺ ሜጋ ዋት በላይ እንደሚያመነጭ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡ በዚህ አመት ከሞላ ጎደል እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ወደ ሚቀጥለው አመት ሊሻጋገር እንደሚችል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህም የሆነው አብዛኛው የውጭ ምንዛሪ በህዳሴ ግድብ ላይ በመዋሉ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ ፋይናንስ ማድረግ በመቻሉ ምናልባት ከአንድ አመት ተኩል እስከ ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኮይሻ ተመርቆ ለስራ ሊውል እንደሚችል ገልጸዋል።