Sports

EBS SPORT – ጣልያናዊው ተከላክይ ጆርጆ ቼሌኒ ከጁቬንቱስ ጋር እንደሚለያይ አስታውቋል

17 አመታትን በቱሪኑ ክለብ ማሳለፍ የቻለው የ 37 አመቱ ተጨዋች በ 2005 ከፊዮረንቲና ጁቬንቱስን መቀላቀሉ የሚታወስ ሲሆን በአሮጊቷ በቆየባቸው አመታትም 9 የሴሪ እንዲሁም 5 የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ማሳካትም ችሏል ፡፡

ተጨዋቹ በኢንተርሚላን ተሸንፈው የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫን ካጡ በኋላ በሰጠው አስተያየትም በመጭው ሰኞ  ከለቡ  በሜዳው በሚያደረግው የመጨረሻ ጨዋታም የጁቪንቱስ ስታድየምን በይፋ እንደሚሰናበት አስታውቋል ቼሌኒ የአውሮፓ አሸናፊዋ ጣልያንና የኮፓ አሜሪካ አሸናፊዋ አርጀንቲና ዌምብሌ ከሚያደርጉት ጨዋታ በኋላም ከሀገሩ ብሄራዊ ቡድን እራሱን እንደሚያገል አስቀድሞ መናገሩም ይታወሳል፡፡

 ተጨዋቹ ስለወደፊት ክለቡ ከቤተሰቡ ጋር ተነጋግሮ ከውሳኔ እንደሚደርስ በመግለጽ ለጁቬንቱስ ሁሉ ነገሩን መስጠቱንና ከዚህ በኋላም ከውጭ ሆኑ ክለቡን በሚገባ እንደሚደግፍ ይፋ አድርጓል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New