EthiopiaNews

የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ

ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ እየተከናወነ መሆኑን የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ማኅበራትና ተቋማት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በንዑሳን ቡድኖች ተከፋፍለው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት በማጠናቀር ላይ መሆናቸውን ያስታወቀው ኮሚሽኑ በቡድን ውይይት የተጠናቀሩ አጀንዳዎች ለጠቅላላ የትግራይ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ቀርበው ሃሳብና አስተያየት ተካቶባቸው የሚፀድቁ ይሆናል ብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews