በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን
ላለፉት 3 አመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሱዳን በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሀገሪቱ ተጠልለው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የሱዳን ዜጎች በጎረቤት አገራት ጥገኝነት ቢጠይቁም ከ862 ሺህ በላይ ስደተኞች ደግሞ በሀገሪቱ ተጠልለው እንደሚገኙም ገልጿል፡፡
ከእነዚህ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚያዙት ደቡብ ሱዳናዊያን መሆናቸውን የጠቀሰው መረጃው ከ135 ሺህ በላይ ኤርትራውያንና ከ68 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሀገሪቱ እንደሚገኙ እና ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን ውስጥ 65 በመቶው በገዳሪፍ እንዲሁም 18 በመቶ የሚሆኑት በብሉ ናይል ግዛት እንደሚገኙም ሪፖርቱ ገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
