EthiopiaNews

‎የንፋስ ኃይል ማመንጫ

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን በዛሬው እለት መመረቃቸውን አስታውቀዋል።

‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቀናል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት ይጨምራል ያሉት ‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይነት ያለው ኃይል ለመገንባት የሚደረገውን ጉዞ ያጠናክራልም ብለዋል።

አክለውም ፕሮጀክቱ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና ያደገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews