EthiopiaNews

ውሳኔ የተሰጠባቸው መዛግብት

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ቀደም ሲል ከቀረቡለት ሕገ መንግሥታዊ የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 109 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሃሳብና አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታወቀ።

11 አባላት ያሉት ጉባዔው ከተወያዬባቸው አቤቱታዎች መካከል አራት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ጥሰት ያለባቸው መሆኑን በማረጋገጡ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲላኩ የወሰነ ሲሆን 96 የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ መወሰኑን ነው ያስታወቀው፡፡

አራት ጉዳዮች ደግሞ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው በቀጣይ እንዲቀርቡ አቅጣጫ የተላለፈ ሲሆን ሌሎች ሶስት አቤቱታዎች ላይ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡ ትእዛዝ መተላለፉን እንዲሁም ሁለት ጉዳዮች ደግሞ እንዲቋረጡ መወሰኑን ይፋ አድርጓል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/