የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝግባ በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ነገ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የመራጮች ምዝገባ እንደሚጠናቀቅ ያስታወሰው ቦርዱ በቀሪው ጊዜያት ዜጎች ለመራጭነት እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርቧል፡፡
እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከ46 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ባወጣው መረጃ ይፋ ያደረገው ምርጫ ቦርድ ለመራጭነት ከተመዘገቡት ውስጥ 21 ሚሊዮን 500 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች እንዲሁም 165 ሺህ አከባቢ የሚሆኑት ደግሞ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡
የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው የመራጮች ምዝገባ ለአንድ ወር እንደሚቆይ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ተይዞለት የነበረው አንድ ወር ሲያልቅ ሁለት ሳምንት ተጨምሮ እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 እንደተራዘመ መገለጹም ይታወሳል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
