InternationalNews

የታይዋን ፕሬዝዳንት እገዳ

ቻይና ለታይዋኑ ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግቴስ አውሮፕላን የአየር ክልላቸውን የዘጉና ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን እንዲሰርዙ ያስገደዱትን 3 የአፍሪካ ሀገራትን ማመስገኗ ተገለጸ።

የታይዋን ፕሬዝዳንት በዓለም ላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱባቸው 12 ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችውን ደቡብ አፍሪካዊቷን ኢስቲዋኒ ለመጎብኘት ነበር ወደ ደቡባዊ አፍሪካ ያቀኑት፡፡

ሆኖም ሲሼልስ፣ ሞሪሺየስና ማዳጋስከር የታይዋኑ ፕሬዝዳንት በአየር ክልላቸው አልፈው ወደ ኢስቲዋኒ እንዲያቀኑ ባለመፍቀዳቸው ፕሬዝዳንቱ የአውሮላናቸውን ፊት አዙረው ወደ አገራቸው ለመመለስ መገደዳቸው ነው የተነገረው፡፡

ማዳጋስከርና ሲሼልስ ይህንን ውሳኔ ለመወሰን የተገደዱት ታይዋንን እንደሀገር ስለማያውቋት መሆኑን መግለጻቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews