የትራምፕ ሽልማትና ቅጣት
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኔቶ ጦር ቃል ኪዳን አባል ሀገራትን የሚቀጡበትና የሚሸልሙበት ዝርዝር ሰነድ ማዘጋጀታቸው ተሰምቷል።
ፖለቲኮ እንደዘገበው ዝርዝሩ በኢራኑ ጦርነት የትኛው አባል አገር ከአሜሪካ ጐን ቆመ የትኛውስ አልተባበረም በሚል ለመለየት የተሰናዳ ሰነድ ነው።
በዝርዝሩ መሰረት መልካም የተባሉት አገራት የአሜሪካን የይሁንታ ሽልማት ሲያገኙ እንቢተኞቹ ደግሞ የእጃቸውን ያገኛሉ ነው የተባለው።
በዝርዝሩ መሰረት ፖላንድና ሩማንያ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ሙገሳ ሲያገኙ ለአሜሪካ የጦር ጄቶች መንደርደሪያ የከለከለችው ስፔን ቅጣት ይጠብቃታል ነው የተባለው።
ብሪታንያና ፈረንሳይም ተባባሪ አይደሉም ከተባሉት ሀገራት ዝርዝር ነው የተቀመጡት። ነገር ግን የትራምፕ ሽልማትና ቅጣት ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ አልታወቀም ተብሏል
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
