EthiopiaNews

የአዋሽ ባንክ አክስዮኖች ምዝገባ

አዋሽ ባንክ አክሲዮኖቹን በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዋዕለ ንዋዮች ገበያ በይፋ ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ይሄን ያለው በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ዋና መስሪያ ቤት ዛሬ በተደረገዉ ይፋዊ የገበያ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ ነው።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጸሐይ ሽፈራዉ ባንኩ ከ54 ሚሊዮን በላይ አክሲዮኖችን ወደ ካፒታል ገበያ ማስገባቱን ተናግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህም ሁኔታ ባለአክሲዮኖች በቀላሉ አክሲዮኖቻቸውን ወደ ጥሬ ገንዘብ እንዲቀይሩ በማስቻል የገበያ ንቁነትን የሚያሳድግ እና ለአገራችን የፋይናንስ የወደፊት ጉዞ የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

ባንኩ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ቀጣይነት ባለዉ መልኩ እንዲተገበሩ የውስጥ ፖሊሲና የአሰራር ማዕቀፎችን የዘረጋ ሲሆን በተጨማሪም የአስተዳደር ማሻሻዎችን አድርጓል፡፡

አዋሽ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ ነባር እና አዲስ ባለአክሲዮኖች የባንኩን አክሲዮኖች ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ የግብይት ስርዓት ውስጥ መገበያየት የሚችሉ መሆኑን አስታዉቋል።

መረጃው ከአዋሽ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv