EthiopiaNews

የህብረቱ ጦርና ፋይናንስ

ኢትዮጵያ የምትመራው የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በሶማሊያ የአል-ሸባብን ስርጭት ለመግታት የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ጦር የፋይናንስ ቀውስን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሊወያይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው ስብሰባ የተልዕኮውን የወደፊት ቆይታ በተመለከተ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘላቂ የፋይናንስ ዋስትና እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀርባል ተብሎም ይጠበቃል።

በሶማሊያ የአል-ሸባብን ስርጭት ለመግታትና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ጦር የፋይናንስ ቀውስ እንደገጠመው ሲገለጽ የሰነበተ ሲሆን ይህም ተልዕኮውን ሊጎዳው እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል፡፡

ተልዕኮው በዚህ ወቅት የተደረገው የ25 በመቶ የበጀት ቅነሳ በአል-ሸባብ ላይ የተመዘገቡ ድሎችን አደጋ ላይ መጣሉም ነው የተነሳው፡፡

ይህም ላለፉት ዓመታት በአልሸባብ ላይ የተመዘገቡ የጸጥታ ድሎችን ወደኋላ ሊመልስ የሚችል የአቅም ክፍተት እየፈጠረ ይገኛል ተብሏል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv