InternationalNews

የአሜሪካና የኢራን የካርታ ጨዋታ

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ በኢራን ላይ ፍፁም የበላይነት የላትም አሉ።

ዋሽንግተንና ቴህራን በቀጣይ ማን በማን ላይ የበላይነት ይኖረዋል በሚል በቃላት እየተጐሻሸሙ ባሉበት ወቅት ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አጋርቺ አሜሪካ በእኛ ላይ የምትመዘው አዲስ ካርድ የለም ያሉት።

በዚህ ውዝግብ መካከልም የአገራቱ ድርድር መራመድ አቅቶት ባለበት ቆሟል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሁሉም ካርድ በእኛ እጅ ነው ያለው ኢራናዊያኑ ከፈለጉ ለድርድር ወይ ወደእኛ ይምጡ ወይ ይደውሉ ማለታቸውን ተከትሎ ነው ኢራን እኔም በእጄ ያለ ካርድ አለኝ ያለችው።

በዚህም ኢራን ትላንት ሆርሙዝ ያለቅድመ ሁኔታ ይከፈት ከዚያ በኋላ ስለኒውክለር መደራደር እንችላለን ያለችበትን አዲስ የሰላም ሃሳብ ማቅረቧ እየተነገረ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv